Phone:

666 888 0000

ኢሜይል:

contact@h4peace.org

ስለ እኛ

ኢትዮጵያውያንን ወደ ሰላም ስለማምጣት

ስለ ተስፋ ለሰላም

ተስፋ ለሰላም ከአማራ እና ከትግራይ ማህበረሰቦች የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን እና በትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ በጋራ የሚመሩት የጋራ ጥረት ነው። ስብስባችን የተወለደው ከዘመናት በፊት በታሪክና በባህላዊ ቅርስ በሚጋሩት በእነዚህ ሁለት ወንድማማች ህዝቦች መካከል እየተባባሰ የመጣው ጠላትነትና ግጭት በጥልቅ ስላሳሰበን ነው። የተስፋ ለሰላም ተቀዳሚ ተልእኮ በአማራና በትግራይ ማኅበረሰቦች መካከል በተለይም በቅርቡ በተካሄደው ጦርነት ወቅት የተፈጠረውን አሳሳቢ የሆነ ጠላትነት ለመፍታትና ወደ ክልሉ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ መንገድ ማመቻቸት ነው።
Hope 4 Peace
ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ግጭት ለዘመናት የቆየ የጋራ ታሪክና ወግ ቀጣይነት ጥያቄ ዉስጥ አስገብቷል

የአስቸኳይ እርቅ አስፈላጊነት

የተስፋ ለሰላም ምስረታ አነሳሽ የሆነው አሁን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በአማራና በትግራይ ማህበረሰቦች መካከል ያለው ጥላቻ ነው። እነዚህ ሁለት ማህበረሰቦች የረዥም ጊዜ ታሪክ ያላቸው፣ እርስ በርስ የተሳሰሩ፣ የጋራ ባህል፣ እምነትና ሃይማኖቶች ያላቸው ናቸው። ይህ ጠላትነት በፖለቲካ ልሂቃን ብቻ ሳይሆን ሌላውም ህዝብም ነክቷል። ግጭቱ በሁለቱም ማህበረሰቦች ከፍተኛ የሰውና የንብረት ውድመት በማድረስ ሀገሪቱን ለከፋ የፖለቲካ ቀውስ ዳርጓል። በሕዝብና በአገሪቷ ህልውና ላይ ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር የውጭ ጣልቃ ገብነትንም ስቧል። እነዚህ ሁለት ማህበረሰቦች በማቀራረብ፣ ሰላምና መረጋጋት ወደ ክልላችን በማምጣት አደጋውን መከላከል አለብን ብለን እናምናለን።
ሰላማዊ ተልእኳችን

ሰላም የሞላባት ነገይቱ ስለመስራት

ተስፋ በሰላም ግልጽና የተከበረ ዓላማ አለው። ይሄውም፣ በእነዚህ ታሪካዊ ቅርበት ባላቸው ማህበረሰቦች መካከል ያለውን ጥላቻና ግጭት ማስቆምና ጤናማ እና ሰላማዊ ግንኙነቶችን መፍጠር ነው። ስብስባችን ሁለቱም ህዝቦች እና መሪዎቻቸው ፖለቲካዊ እና ሌሎች ልዩነቶቻቸውን በውይይት፣ በድርድር እና በህጋዊ መንገድ የሚፈቱበት ሰላማዊ የፖለቲካ ምህዳር መፍጠር ይፈልጋል። የችግሩን ፖለቲካዊ ምንጭ በመገንዘብም ተስፋ ለሰላም ምንም አይነት የፖለቲካ አጀንዳም ሆነ የስልጣን ጥማት እንደሌለው አበክረን መግለጽ እንወዳለን። በአማራና በትግራይ ማህበረሰብ መካከል ሰላም እንዲሰፍንና የተስተካከለ ግንኙነት እንዲፈጠር ገንቢ ሚና ለመጫወት ብቻ የተቋቋመና የተወሰነ አጀንዳ ያለው፣ ቋሚ መዋቅርም ሆነ ህጋዊ እውቅና የሌለው ስብስብ ነው።