የአገዛዙ ህዝብን ከህዝብ የማዋጋት ዳግም ሴራ ሊከሽፍ ይገባል!
የአገዛዙ ህዝብን ከህዝብ የማዋጋት ዳግም ሴራ ሊከሽፍ ይገባል! ከተስፋ ለሰላም የተሰጠ መግለጫ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣት በኋላ በኢትዯጵያ ውስጥ በሺ የሚቆጠሩ ግጭቶች ተከስተዋል። በሰሜኑ የአገራችን ክፍልና በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ህዝብ ጨራሽ ጦርነቶች ተካሂደዋል፣ አሁንም በመካሄድ ላይ ይገኛሉ። ከአንድ አመት በፊት በፕሪቶርያው ስምምነት የቆመው የአማራና የአፋር ክልሎችን ጨምሮ በዋናነት በትግራይ በተካሄደው ጦርነት ብቻ በታሪካችን አይተነው በማናውቅ መጠን ከ1 ሚሊየን በላይ የሆነ ህዝብ እንደሞተና ከ4 ሚሊየን የበለጠ ህዝብ ከመኖሪያ ቀየው እንደተፈናቀለ ይገመታል። እነዚህ